Susanna Wesley 1669–1742
1 መጽሐፍ በቤተ መጻሕፍቱ ውስጥበ1669 በእንግሊዝ አገር በለንደን የተወለደችው ሱዛና ዌስሊ የሜቶዲዝም መሥራቾች የሆኑት የጆንና የቻርልስ ዌስሊ እናት ናት። ቀናተኛ የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን አማኝና የአሥራ ዘጠኝ ልጆች እናት የነበረችው ሱዛና (ከእነርሱ አሥሩ ለአቅመ አዳም ደርሰዋል) ለልጆቿ ጥብቅ የሃይማኖት ትምህርት የሰጠች ሲሆን፣ የዕለት ተዕለት የጸሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሥርዓትን አቋቁማለች። የገንዘብ ችግርና የባሏ ከቤት መራቅ ቢገጥማትም በመንፈሳዊ ሕይወቱ የጸና ቤተ ሰብ ጠብቃ አቆይታለች።







