ምዕራፍ 1 · 1 ደቂቃ ንባብ
መቅድም
ወጣት ክርስቲያኖች በቀላሉ ሊገነዘቡት የሚችሉትን፣ የክርስትና ሕይወት ሳይከናወን የማይቀርበትን ያንን አቋም እንዲይዙ የሚረዳቸውን ነገር ለመጻፍ ልቤ ተሳበ። የክርስትና ሕይወት ዋና ዋና ፈተናዎችና ውድቀቶች አንዳቸውም እንኳ እዚህ መልስ ያላገኙ አይመስሉም። የጌታ ኢየሱስ ቅርበት፣ ሁሉን የሚበቃ መሆኑና ታማኝነቱ፣ እንዲሁም የእምነት ሕይወት ተፈጥሮአዊነትና ፍሬያማነት በዚህ ምሳሌ እጅግ ተገልጠዋልና፣ አንድ ሰው በድፍረት፦ ምሳሌው ወደ ልብ ይግባ፤ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ሊል የሚችል ይመስላል።
የተባረከው ጌታ በረከቱን ይስጥ። የእግዚአብሔርን የራሱን ትምህርት እየተጠባበቅን የወይን ግንዱን ምሥጢር በአምልኮ መንፈስ እንድናጠና ያስተምረን።
ምዕራፍ 1 ተጠናቋል
መቅድም