ምዕራፍ 5 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
በሥራ አስተዋይ መሆን
ለሚመጣብህ ስሜትና አሳብ ሁሉ እጅህን አትስጥ፤ ነገር ግን ነገሮችን በእግዚአብሔር ፈቃድ ብርሃን በጥንቃቄና በትዕግሥት መርምር። ያሳዝናል፤ ብዙ ጊዜ እጅግ ደካሞች ከመሆናችን የተነሣ ስለ ሌሎች ከመልካም ይልቅ ክፉን እናምናለን፤ እንናገራለንም። ፍጹማን ሰዎች ግን የሰው ድካም ወደ ክፉ የሚያዘነብልና በንግግርም ሊገለጥ የተዘጋጀ መሆኑን ስለሚያውቁ ወሬ የሚያመላልስን ሁሉ ቶሎ አያምኑም።
በችኮላ አለመሥራት፣ በራስ አሳብ በግትርነት አለመጽናት፣ ሰዎች የሚሉትን ሁሉ አለማመንና የሰሙትንም ሐሜት አለማዛመት ታላቅ ጥበብ ነው።
ጠቢብና ሕሊናውን ከሚጠብቅ ሰው ጋር ተመካከር። የራስህን ዝንባሌ ከመከተል ይልቅ ከአንተ የሚበልጡትን ምክር ፈልግ።
መልካም ሕይወት ሰውን በእግዚአብሔር ዘንድ ጠቢብ ያደርገዋል፤ በብዙ ነገርም ልምድ ይሰጠዋል፤ ይበልጥ ትሑትና ለእግዚአብሔር ይበልጥ የሚገዛ በሆነ መጠን በነገር ሁሉ ይበልጥ ጠቢብና ይበልጥ ሰላማዊ ይሆናልና።
ምዕራፍ 5 ተጠናቋል
በሥራ አስተዋይ መሆን