ምዕራፍ 7 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
ወደ ምድረ በዳ ሄዶ በመንገድ ላይ ፈተናዎችን ድል ያደርጋል
11. በማግሥቱም ለእግዚአብሔር አገልግሎት ይበልጥ ተግቶ ወጣ፤ ቀድሞ ያገኘውን ሽማግሌም አግኝቶ ከእርሱ ጋር በምድረ በዳ እንዲኖር ለመነው። ያም ሽማግሌ ከዕድሜው ብዛትና ገና እንዲህ ያለ ልማድ ስላልነበረ እምቢ ባለ ጊዜ፣ አባ እንጦንስ ራሱ ወዲያውኑ ወደ ተራራው ጉዞ ጀመረ። ጠላትም እንደ ገና ትጋቱን አይቶ ሊያሰናክለው ፈልጎ ታላቅ የብር ሳሕን የሚመስል ነገር በመንገዱ ላይ ጣለለት። አባ እንጦንስ ግን የክፉውን ተንኰል አይቶ ቆመ፤ ሳሕኑንም ተመልክቶ በውስጡ ያለውን ዲያብሎስ እንዲህ ብሎ አሳፈረው፦ «በምድረ በዳ ሳሕን ከወዴት መጣ? ይህ መንገድ የተረገጠ አይደለም፤ የመንገደኛም ዱካ በዚህ የለም፤ ከትልቅነቱ የተነሣ ሳይታወቅ ሊወድቅ አይችልም ነበር፤ የጣለውም ሰው ተመልሶ ቢፈልገው ባገኘው ነበር፤ ምድረ በዳ ነውና። ይህ የዲያብሎስ ተንኰል ነው። አንተ ክፉ ሆይ፣ በዚህ ዓላማዬን አታሰናክለውም፤ ከአንተ ጋር ይጥፋ።» አባ እንጦንስም ይህን ባለ ጊዜ ጢስ ከእሳት ፊት እንደሚጠፋ ተሰወረ።
ምዕራፍ 7 ተጠናቋል
ወደ ምድረ በዳ ሄዶ በመንገድ ላይ ፈተናዎችን ድል ያደርጋል