ምዕራፍ 40 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
መናፍስትን የመለየት ጸጋውና ለሁሉ መካሪ መሆኑ
88. በአባ እንጦንስ ተጋድሎ ውስጥ አስደናቂው ነገር ይህ ነበርና፤ ቀደም ብዬ እንደ ተናገርሁ መናፍስትን የመለየት ጸጋ ስለ ነበረው እንቅስቃሴያቸውን ያውቅ ነበር፤ ከእነርሱም እያንዳንዱ ኀይሉን ወዴት እንደሚያዞርና ጥቃቱን በምን በኩል እንደሚሰነዝር አላጣውም ነበር። እርሱ ራሱ በእነርሱ አለመታለሉ ብቻ ሳይሆን፣ በጥርጣሬ የታወኩትንም እያበረታታ ሴራቸውን እንዴት ድል እንደሚያደርጉ ያስተምራቸው ነበር፤ ያደሩባቸውንም የአጋንንት ድካምና ተንኰል ይነግራቸው ነበር። ስለዚህ እያንዳንዱ በእርሱ ለውጊያ እንደ ተዘጋጀ ሆኖ የዲያብሎስንና የአጋንንቱን ሴራ በድፍረት እየተቋቋመ ከተራራው ይወርድ ነበር። እጮኛ የነበራቸው ስንት ቈነጃጅት አባ እንጦንስን ከሩቅ ብቻ አይተው ስለ ክርስቶስ ብለው ደናግል ሆነው ቀሩ! ሰዎችም ከባዕድ አገሮች ደግሞ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፤ እንደ ሌሎቹም ሁሉ ጥቅም አግኝተው በአባት እንደ ተሸኙ ሆነው ይመለሱ ነበር። በእርግጥም በሞተ ጊዜ ሁሉም አባታቸውን እንዳጡ ሆነው ምክሩንና ተግሣጹን እየጠበቁ እርሱን በማስታወስ ብቻ ራሳቸውን ያጽናኑ ነበር።
ምዕራፍ 40 ተጠናቋል
መናፍስትን የመለየት ጸጋውና ለሁሉ መካሪ መሆኑ