ምዕራፍ 15 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
አንዲትን ሴት ከክፉ መንፈስ እንዴት እንዳዳናት
48. ስለዚህ ወደ ውስጥ ገብቶ ከዚያ በኋላ እርሱ ራሱ እንዳይወጣ፣ ማንንም እንዳያስገባ ጊዜ ለመወሰን በቈረጠ ጊዜ፣ ማርቲንያኖስ የተባለ አንድ የጦር አለቃ መጥቶ አባ እንጦንስን አወከው። ክፉ መንፈስ የሚያሠቃያት ሴት ልጅ ነበረችውና። በሩንም ለረጅም ጊዜ እያንኳኳ ወጥቶ ስለ ልጁ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ሲለምነው፣ አባ እንጦንስ ሊከፍትለት ሳይወድድ ከላይ ሆኖ ወደ ውጭ ተመልክቶ እንዲህ አለው፦ «አንተ ሰው፣ ስለ ምን ትጠራኛለህ? እኔ ደግሞ እንደ አንተ ሰው ነኝ። ነገር ግን በማገለግለው በክርስቶስ ብታምን፣ ሂድ፤ እንደ እምነትህም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፤ ይሆንልሃልም።» ወዲያውም አምኖና ክርስቶስን እየጠራ ሄደ፤ ልጁንም ከዲያብሎስ ነጽታ ተቀበላት። «ፈልጉ፥ ይሰጣችሁማል» የሚለው ጌታ በአባ እንጦንስ በኩል ሌሎች ብዙ ነገሮችንም አደረገ። ከሕመምተኞቹ ብዙዎቹ በሩን ባልከፈተላቸው ጊዜ ከበዓቱ ውጭ ያድሩ ነበርና፤ በእምነታቸውና በቅን ጸሎታቸውም ይፈወሱ ነበር።
ምዕራፍ 15 ተጠናቋል
አንዲትን ሴት ከክፉ መንፈስ እንዴት እንዳዳናት