ምዕራፍ 55 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
የእንዲህ ያለ ፍቅር ምሳሌዎች
ከአሕዛብ መካከል አንዳንድ ምሳሌዎችን እናቅርብ፦ ብዙ ነገሥታትና መኳንንት በቸነፈር ዘመን የሟርት ቃል ከመከራቸው በኋላ በገዛ ደማቸው የአገራቸውን ሰዎች [ከጥፋት] ያድኑ ዘንድ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል። ብዙዎች በከተሞቻቸው ውስጥ ዓመፅ ያከትም ዘንድ ከገዛ ከተሞቻቸው ወጥተዋል። ከእኛም መካከል ሌሎችን ይቤዡ ዘንድ ራሳቸውን ለእስራት አሳልፈው የሰጡ ብዙዎችን እናውቃለን። ብዙዎችም ስለ ራሳቸው በተቀበሉት ዋጋ ለሌሎች ምግብ ያቀርቡ ዘንድ ራሳቸውን ለባርነት ሰጥተዋል። ብዙ ሴቶችም በእግዚአብሔር ጸጋ በርትተው ብዙ የጀግንነት ሥራ ሠርተዋል። ብፅዕት ዮዲት ከተማዋ በተከበበች ጊዜ ወደ ባዕዳን ሰፈር ትወጣ ዘንድ ሽማግሌዎችን ፈቃድ ለመነች፤ ራስዋንም ለአደጋ አጋልጣ ለአገርዋና በዚያን ጊዜ ለተከበበው ሕዝብዋ ስለ ነበራት ፍቅር ወጣች፤ ጌታም ሆሎፎርኒስን በሴት እጅ አሳልፎ ሰጠው። አስቴርም ደግሞ በእምነት ፍጽምት ሆና የእስራኤልን አሥራ ሁለቱን ነገዶች ከሚመጣባቸው ጥፋት ታድን ዘንድ ራስዋን ከዚህ ባላነሰ አደጋ ላይ ጣለች። ሁሉን የሚያየውን የዘላለሙን አምላክ በጾምና ራስን በማዋረድ ለመነችው፤ እርሱም የነፍስዋን ትሕትና አይቶ ስለ እነርሱ ራስዋን ለአደጋ የሰጠችላቸውን ሕዝብ አዳነ።
ምዕራፍ 55 ተጠናቋል
የእንዲህ ያለ ፍቅር ምሳሌዎች