ምዕራፍ 54 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
በፍቅር የተሞላ ሰው ማናቸውንም ጉዳት ይቀበላል
እንግዲህ ከእናንተ መካከል ልበ ሰፊ ማን ነው? ርኅሩኅ ማን ነው? በፍቅር የተሞላ ማን ነው? እንዲህ ብሎ ይናገር፦ «በእኔ ምክንያት ዓመፅና አለመስማማት መለያየትም ተነሥተው ከሆነ እሄዳለሁ፤ ወደምትፈልጉት ስፍራ ሁሉ እርቃለሁ፤ ብዙዎቹ የሚያዝዙትንም ሁሉ አደርጋለሁ፤ ብቻ የክርስቶስ መንጋ በላዩ ከተሾሙት ሽማግሌዎች ጋር በሰላም ይኑር።» እንዲህ የሚያደርግ ሰው በጌታ ዘንድ ለራሱ ታላቅ ክብርን ያገኛል፤ ስፍራም ሁሉ ይቀበለዋል። «ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና።» እግዚአብሔርን በመምሰል የማይጸጸቱበትን ኑሮ የሚኖሩ ሰዎች ይህን አድርገዋል፤ ወደ ፊትም ዘወትር ያደርጋሉ።
ምዕራፍ 54 ተጠናቋል
በፍቅር የተሞላ ሰው ማናቸውንም ጉዳት ይቀበላል