ምዕራፍ 48 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
ወደ ወንድማማች ፍቅር ኑሮ እንመለስ
እንግዲህ ይህን [ነገር] ፈጥነን እናስወግድ፤ በጌታም ፊት ወድቀን በምሕረቱ ከእኛ ጋር እንዲታረቅ፥ ወደ ቀድሞው ወደ ተገባውና ወደ ቅዱሱ የወንድማማች ፍቅር ኑሮአችንም እንዲመልሰን በእንባ እንለምነው። [እንዲህ ያለው ኑሮ] ሕይወትን ለማግኘት የተከፈተ የጽድቅ ደጅ ነውና፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ «የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ ጻድቃን ወደ እርስዋ ይገባሉ።» እንግዲህ ብዙ ደጆች የተከፈቱ ቢሆኑም ይህ የጽድቅ ደጅ በክርስቶስ ያለው ደጅ ነው፤ በእርሱ የገቡና መንገዳቸውን በቅድስናና በጽድቅ ያቀኑ፥ ሁሉንም ያለ ሁከት የሚያደርጉ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። ሰው የታመነ ይሁን፤ እውቀትን በመናገር ብርቱ ይሁን፤ ቃላትን በመለየት ጠቢብ ይሁን፤ በሥራው ሁሉ ንጹሕ ይሁን፤ ሆኖም [በእነዚህ ነገሮች] ከሌሎች የሚበልጥ በመሰለ መጠን ይበልጥ ትሑት ሊሆን፥ የራሱን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሁሉን የጋራ ጥቅም ሊፈልግ ይገባዋል።
ምዕራፍ 48 ተጠናቋል
ወደ ወንድማማች ፍቅር ኑሮ እንመለስ