ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈው የቀሌምንጦስ የመጀመሪያ መልእክት
ከዚህ ምንጭ በጥንት ዘመናት ብዙ ክፋቶች ፈልቀዋል

ምዕራፍ 4 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ

ከዚህ ምንጭ በጥንት ዘመናት ብዙ ክፋቶች ፈልቀዋል

እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፦ «ከብዙ ቀንም በኋላ ቃየል ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አመጣ፤ አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስባቸው አመጣ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መባው ተመለከተ፤ ወደ ቃየልና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየልም እጅግ አዘነ፤ ፊቱም ጠቈረ። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው፦ ለምን አዘንህ? ለምንስ ፊትህ ጠቈረ? በቅን ብታቀርብ፥ በቅን ግን ባትከፍል፥ አልበደልህምን? ዝም በል፤ መባህ ወደ አንተ ይመለሳል፤ አንተም እንደ ገና ትገዛዋለህ። ቃየልም ወንድሙን አቤልን፦ ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።» ወንድሞች ሆይ፥ ቅናትና ምቀኝነት ወንድምን ወደ መግደል እንዴት እንዳደረሱ ታያላችሁ። ደግሞም አባታችን ያዕቆብ ከቅናት የተነሣ ከወንድሙ ከዔሳው ፊት ሸሸ። ቅናት ዮሴፍን እስከ ሞት ድረስ እንዲሰደድና ወደ ባርነት እንዲገባ አደረገው። ቅናት ሙሴን ከወገኑ ሰው፦ «አንተን በእኛ ላይ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ትናንትና የግብፁን ሰው እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትወዳለህን?» የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ፊት እንዲሸሽ አስገደደው። ከቅናት የተነሣ አሮንና ማርያም ከሰፈሩ ውጭ ለመኖር ተገደዱ። ቅናት በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ ላይ ባስነሡት ሁከት ምክንያት ዳታንንና አቤሮንን በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል አወረዳቸው። ከቅናት የተነሣ ዳዊት በባዕዳን መጠላት ብቻ ሳይሆን በእስራኤል ንጉሥ በሳኦልም ተሳደደ።

ገጽ 1 / 1 · 1 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል
ቀዳሚ ቀጣይ