ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈው የቀሌምንጦስ የመጀመሪያ መልእክት
እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን እናድርግ

ምዕራፍ 30 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ

እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን እናድርግ

እንግዲህ የቅዱሱ እድል ፈንታ ስለ ሆንን፣ ክፉ ንግግርን ሁሉ፣ አስጸያፊና ርኩስ መተቃቀፍን ሁሉ፣ ስካርን ሁሉ፣ ሁከት መሻትን፣ አስጸያፊ ምኞትን ሁሉ፣ የተጠላ ምንዝርንና የተረገመ ትዕቢትን እየራቅን ለቅድስና የሚገባውን ሁሉ እናድርግ። «እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል» ይላልና [መጽሐፍ]። እንግዲህ ከእግዚአብሔር ጸጋ ከተሰጣቸው ጋር እንተባበር። ራሳችንን ዘወትር እየገዛን፣ ከሹክሹክታና ከሐሜት ሁሉ ርቀን እየቆምን፣ በቃላችን ሳይሆን በሥራችን እየጸደቅን ስምምነትንና ትሕትናን እንልበስ። [መጽሐፍ] እንዲህ ይላልና፦ «ብዙ የሚናገር ብዙ መልስ ደግሞ ይሰማል። በንግግር የፈጠነስ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ይቈጥራልን? ጥቂት ዘመን የሚኖር ከሴት የተወለደ የተባረከ ነው፤ ብዙ አትናገር።» ምስጋናችን በእግዚአብሔር ይሁን እንጂ ከራሳችን አይሁን፤ እግዚአብሔር ራሳቸውን የሚያመሰግኑትን ይጠላልና። ለመልካም ሥራችን ምስክርነት፣ በጻድቃን አባቶቻችን ዘንድ እንደ ነበረው፣ በሌሎች ይሰጥ። ድፍረትና ኩራት ትምክህትም በእግዚአብሔር ለተረገሙት ናቸው፤ ልከኝነትና ትሕትና የዋህነትም በእርሱ ለተባረኩት ናቸው።

ገጽ 1 / 1 · 1 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል
ቀዳሚ ቀጣይ