ምዕራፍ 29 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
እኛም በንጹሕ ልብ ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ
እንግዲህ ንጹሕና ያልረከሱ እጆችን ወደ እርሱ እያነሣን፣ ከመረጣቸው ሰዎች በረከት ተካፋዮች ያደረገንን ቸርና መሐሪ አባታችንን እየወደድን በመንፈስ ቅድስና ወደ እርሱ እንቅረብ። እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፦ «ልዑል አሕዛብን በከፈለ ጊዜ፥ የአዳምን ልጆች በበተነ ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር የአሕዛብን ድንበር ወሰነ። ሕዝቡ ያዕቆብ የጌታ እድል ፈንታ ሆነ፥ እስራኤልም የርስቱ ዕጣ።» በሌላም ስፍራ [መጽሐፍ] እንዲህ ይላል፦ «እነሆ፥ ሰው ከአውድማው በኵራትን እንደሚወስድ፥ ጌታ ከአሕዛብ መካከል ለራሱ ሕዝብን ይወስዳል፤ ከዚያም ሕዝብ ቅዱሰ ቅዱሳን ይወጣል።»
ምዕራፍ 29 ተጠናቋል
እኛም በንጹሕ ልብ ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ