ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈው የቀሌምንጦስ የመጀመሪያ መልእክት
ከቅናት የተነሣ ሁከት ከተነሣ በኋላ የቤተ ክርስቲያን አሳዛኝ ሁኔታ

ምዕራፍ 3 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ

ከቅናት የተነሣ ሁከት ከተነሣ በኋላ የቤተ ክርስቲያን አሳዛኝ ሁኔታ

ክብርና ደስታ ሁሉ ተሰጣችሁ፤ ያን ጊዜም፦ «ውዴ በላ፥ ጠጣም፤ ሰፋ፥ ወፈረም፥ ረገጠም» ተብሎ የተጻፈው ተፈጸመ። ከዚህም ፉክክርና ቅናት፣ ጠብና ሁከት፣ ስደትና ሥርዓት አልበኝነት፣ ጦርነትና ምርኮ ፈለቁ። እንዲሁ ከንቱዎቹ በተከበሩት ላይ፣ ስም የሌላቸው በታወቁት ላይ፣ ሰነፎች በጥበበኞች ላይ፣ ጐበዞችም በዕድሜ በገፉት ላይ ተነሡ። ስለዚህ ምክንያት ጽድቅና ሰላም አሁን ከእናንተ እጅግ ርቀዋል፤ እያንዳንዱ የእግዚአብሔርን ፍርሃት ትቶአልና፤ በእምነቱም ታውሮአል፤ እርሱ በሠራቸው ሥርዓቶች አይመላለስም፤ ለክርስቲያንም የሚገባውን አያደርግም፤ ነገር ግን ዓመፀኛና ኃጢአተኛ የሆነውን ቅናት እንደ ገና እየለማመደ በገዛ ክፉ ምኞቱ ይመላለሳል፤ በዚህ ቅናት ሞት ራሱ ወደ ዓለም ገብቶአልና።

ገጽ 1 / 1 · 1 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል
ቀዳሚ ቀጣይ