ምዕራፍ 17 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
የትሕትና ምሳሌዎች የሆኑ ቅዱሳን
የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው እየዞሩ የክርስቶስን መምጣት የሰበኩትን ደግሞ እንምሰል፤ ከነቢያት መካከል ኤልያስን፣ ኤልሳዕንና ሕዝቅኤልን፣ እንዲሁም [በመጽሐፍ] እንደ እነርሱ የተመሰከረላቸውን ሌሎቹን ማለቴ ነው። አብርሃም እጅግ የተከበረ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ፤ እርሱ ግን የእግዚአብሔርን ክብር በትጋት እየተመለከተ በትሕትና፦ «እኔ ትቢያና አመድ ብቻ ነኝ» አለ። ደግሞም ስለ ኢዮብ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ «ኢዮብ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት፥ እውነተኛ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ራሱንም ከክፉ ነገር ሁሉ የሚጠብቅ ሰው ነበረ።» እርሱ ግን ራሱን እየከሰሰ፦ «ሕይወቱ አንድ ቀን ብቻ እንኳ ቢሆን ከርኵሰት ንጹሕ የሆነ ሰው የለም» አለ። ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ የታመነ ተባለ፤ በእርሱም አማካይነት እግዚአብሔር ግብፅን በመቅሠፍትና በሥቃይ ቀጣ። እርሱ ግን እንዲህ እጅግ የተከበረ ቢሆንም የትዕቢት ቃል አልተናገረም፤ ነገር ግን መለኮታዊው ቃል ከቍጥቋጦው ውስጥ በመጣለት ጊዜ፦ «የምትልከኝ እኔ ማን ነኝ? እኔ ደካማ ድምፅና ኰልታፋ ምላስ ያለኝ ሰው ነኝ» አለ። ደግሞም፦ «እኔ እንደ ድስት ጢስ ብቻ ነኝ» አለ።
ምዕራፍ 17 ተጠናቋል
የትሕትና ምሳሌዎች የሆኑ ቅዱሳን