ምዕራፍ 10 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
ከላይ ያለው ቀጣይ
«ወዳጅ» የተባለው አብርሃም ለእግዚአብሔር ቃል ስለ ታዘዘ ታማኝ ሆኖ ተገኘ። እርሱ በመታዘዝ ከአገሩ፣ ከዘመዶቹና ከአባቱ ቤት ወጣ፤ ይኸውም ትንሽ ምድርን፣ ደካማ ቤተሰብንና ታናሽ ቤትን ትቶ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሎች ይወርስ ዘንድ ነው። እግዚአብሔር እንዲህ ብሎታልና፦ «ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፥ አንተም ብሩክ ትሆናለህ። የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።» ደግሞም ከሎጥ በተለየ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ «ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና። ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ [ስለዚህ] ሰው የምድርን አሸዋ ሊቈጥር ቢችል ዘርህ ደግሞ ይቈጠራል።» ደግሞም [መጽሐፍ] እንዲህ ይላል፦ «እግዚአብሔር አብራምን ወደ ውጭ አወጣውና እንዲህ አለው፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠራቸው፤ ዘርህም እንዲሁ ይሆናል። አብራምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።» ከእምነቱና ከእንግዳ ተቀባይነቱ የተነሣ በእርጅናው ልጅ ተሰጠው፤ በመታዘዝም እግዚአብሔር ካሳየው ተራሮች በአንዱ ላይ ልጁን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው።
ምዕራፍ 10 ተጠናቋል
ከላይ ያለው ቀጣይ