ምዕራፍ 11 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
የዚሁ ቀጣይ
ከእንግዳ ተቀባይነቱና እግዚአብሔርን ከመምሰሉ የተነሣ፣ በዙሪያው ያለው አገር ሁሉ በእሳትና በዲን በተቀጣ ጊዜ ሎጥ ከሰዶም ዳነ፤ ጌታም በዚህ በእርሱ ተስፋ የሚያደርጉትን እንደማይተዋቸው፣ ከእርሱ የሚርቁትን ግን ለቅጣትና ለሥቃይ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ገለጠ። ከእርሱ ጋር የወጣችው የሎጥ ሚስት ከእርሱ የተለየ አሳብ ስለ ነበራትና [ስለ ተሰጣቸው ትእዛዝ] ከእርሱ ጋር በአንድ ልብ ስላልጸናች እስከ ዛሬ ድረስ የጨው ዓምድ ሆና ምሳሌ ተደረገች። ይህም የተደረገው ሁለት ልብ ያላቸውና በእግዚአብሔር ኃይል የሚጠራጠሩ በራሳቸው ላይ ፍርድን እንደሚያመጡ፣ ለሚመጡትም ትውልዶች ሁሉ ምልክት እንደሚሆኑ ሁሉም ያውቁ ዘንድ ነው።
ምዕራፍ 11 ተጠናቋል
የዚሁ ቀጣይ