ጸሎት — የሕይወት ትርታ
የጸሎትን መንፈስ መኮትኮት

ምዕራፍ 5 · 2 ደቂቃ ንባብ

የጸሎትን መንፈስ መኮትኮት

ሆን ብለህ የምትኮተኩተው ነገር ሁሉ ያድጋል!

የጸሎት መንፈስ ማን ነው?

«እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል።» ሮሜ 8:26። የጸሎት መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ስለ እኛ የሚማልደውም እርሱ ነው። በእኛ አማካይነት በሕይወታችን ውስጥ የጸሎትን ከባቢ ይጠብቃል። ሁሉም ሰው እርሱ ሊኖረው ይገባል! ብናስተውልም ባናስተውልም እርሱ በእኛ ውስጥ በኃይል ይሠራል፤ ያለ እርሱም ምንም ነገር በፍጹምነት ሊደረግ አይችልም።

እርሱን የምንቀበለውና የምንጋብዘው በመሻት ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በሕይወታችን እንደ ተቀበልነው በዚያው መንገድ፥ ማለትም በእምነት እንቀበለዋለን። መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት አንድ ተግባር ልትፈጽም አትችልም፤ መልካም ሥራዎች እንኳ እንዲመጣ ወይም እንዲሞላህ ሊያደርጉት አይችሉም። በመሻትና በእምነት ነው።

መንፈስ ቅዱስ በእውነት ድንቅ ነው። ከተጠማህ ያረካሃል። ሳታቋርጥ ስትጸልይ ራስህን ታገኘዋለህ። ወደ ራእዮቹ፣ ዕቅዶቹና ዓላማዎቹ ይመራሃል። በጸሎት በአንተ በኩል ራሱን ይገልጣል፤ አንተም እርሱ እየሠራ እንዳለ ታውቃለህ! በነገር ሁሉ ፍጹም መሪ ስለ ሆነ ሁሉም ሰው የጸሎት መንፈስ ሊኖረው ያስፈልገዋል።

አንድ ሰው እንዲህ ይል ይሆናል፦ «ጸልዬ የጸሎት መንፈስ በሕይወቴ ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርግ ጋብዤዋለሁ፤ ነገር ግን ምንም ለውጥ አላይም።» ለዚህ ልጆችዋ ጌታ ኢየሱስን እንዲቀበሉና ዳግመኛ እንዲወለዱ በምትፈልግ አንዲት እናት ምሳሌ እመልሳለሁ። እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነው ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ እንዲችሉ ልጆችዋ ኢየሱስን እንዲያዩ ትጸልያለች። ችግሩ ከየት እንደሚመጣ አስተዋልህ? ችግሩ ያለው በጸሎቱ ምክንያት/ዓላማ ላይ ነው። ነፍሳት ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጸለይ ድንቅ ነገር ነው፤ ነገር ግን ዓላማው ለግል ደስታ ከሆነ ራስ ወዳድነት ስለ ሆነ ኃይለኛ ጸሎት መሆኑ ይቀራል። «ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።»

ያዕቆብ 4:3። ትኩረታችን በዘላለማዊነት ላይ መሆን አለበት። ምናልባት አንድ ሰው ለጸሎት መንፈስ ከጸለየ በኋላም እንኳ ምንም ለውጥ ያላየው በዚህ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለ ወዳጅህ፣ ስለ አስተማሪህ፣ ስለ እኅትህ ወይም ስለ ሌላ ማንኛውም ሰው ስትጸልይ፥ ለምትጸልይበት ነገር ትክክለኛ ምክንያት እንዲኖርህ ሁልጊዜ አስታውስ።

ታዲያ የጸሎትን መንፈስ እንዴት ልንኮተኩት እንችላለን? ከመንፈስ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እንዴት ልንጠቀም እንችላለን? የጸሎትን መንፈስ እንዴት ልንንከባከብ እንችላለን?

1. ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይ፣ እምነት በመያዝና በማየት ሳይሆን በእምነት እንደምትመላለስ በማሳየት። ይህ ማለት የሌሉትን ነገሮች እንዳሉ አድርገህ ልትጠራቸው ትችላለህ ማለት ነው። ኃይሉ በአንተ ውስጥ ስላለ ሁኔታው እንዲለወጥ ልታዝዝ ትችላለህ። ከ10,000 ሠራዊት ትበረታለህ! ከወባ፣ ከጨጓራ ቁስለት፣ ከካንሰር፣ ከሄፓታይተስ፣ ከማሕፀን እጢ፣ ከኤች አይ ቪ፣ ከሲክል ሴል፣ ከዕጢዎችና ከሌላ ማንኛውም ሕመም ወይም በሽታ ትበረታለህ። ጌታ ይመስገን! በሕይወትህ ለውጥ የማምጣት ኃይል ስላለህ በመንፈስ ጸልይ፤ ምሥጢራትንም ልቀቅ።

2. የጸሎትን መንፈስ የምንኮተኩተው በእግዚአብሔር ቃል ላይ በማሰላሰል ነው። በቃሉ አማካይነት መንፈስ ቅዱስ ሊነሣሣና አጥብቀን እንድንጸልይ ሊያደርገን ይችላል። ቃሉን ባነበብህ መጠን ይበልጥ ታውቀዋለህ፤ ያወቅኸውንም በሥራ ላይ ማዋልና ሁልጊዜ በእርሱ ላይ ማሰላሰል ከቻልህ፥ ፈጽሞ ተስፋ አትቆርጥም ወይም አትጎዳም። በእግዚአብሔር ቃል እየተመገብህና በእርሱ እየሠራህ ስለ ሆነ ሁልጊዜ ታድጋለህ፤ ይህም የጸሎትን መንፈስ ያነሣሣል። እንዲህ ባለ ከባቢ ውስጥ በሽታዎች ሊስፋፉ አይችሉም፤ ሕመሞችም አይችሉም፤ ኀዘንም፣ ኩነኔም፣ ጭንቀትም አይችሉም!

ምዕራፍ 5 ተጠናቋል

የጸሎትን መንፈስ መኮትኮት

ገጽ 1 / 1 · 2 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል