ምዕራፍ 1 · 1 ደቂቃ ንባብ
የደራሲው የሕይወት ታሪክ
ጋሬዝና ባለቤቱ አን ሁለቱም የተወለዱትና ያደጉት በዌልስ ነው። ጋሬዝ ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ በፊዚክስ የመጀመሪያ ዲግሪውን በክብር እና የትምህርት ዲፕሎማ ከተቀበለ በኋላ በ1961 ተጋቡ። በ1975 ወደ ካናዳ ተሰደዱ፤ በዚያም ጋሬዝ በመረጠው ሙያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህር ሆኖ ቀጠለ። በ1979 በኦንታሪዮ ግዛት በምትገኘው በኪችነር ከተማ፣ በክርስቲያን ኤንድ ሚሽነሪ አላያንስ ሥር ያለችን ቤተ ክርስቲያን በእረኝነት እንዲያገለግል ተጋበዘ።
ከአራት ዓመት በኋላ ወደ ቪክቶሪያ፣ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ጥሪ ቀረበለት፤ በዚያም ለቀጣዮቹ ስምንት ዓመታት በእረኝነት አገለገለ፤ እስከ ዛሬም የሚኖሩት እዚያው ነው።
በ1990 ጋሬዝ በአውሮፓና በምዕራብ አፍሪካ መካከል በምትሠራው «ኤም/ቪ አናስታሲስ» በተባለችው የምሕረት መርከብ ላይ ቄስ ሆኖ እንዲያገለግል ተጋበዘ።
በዚያም እርሱና አን የመርከቧን ሠራተኞች አገለገሉ፤ በአብያተ ክርስቲያናት፣ በፓስተሮች ሴሚናሮችና በሚስዮናውያን ጉባኤዎች ላይ ለመናገርም ብዙ ዕድል አገኙ። በ1994 መርከቧን ከለቀቀ ወዲህ ጋሬዝ በደቀ መዝሙርነት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቶችና በልዩ ልዩ ጉባኤዎች እያስተማረ በብዙ ስፍራዎች ተጉዟል። ጋሬዝና አን ሦስት ሴቶች ልጆች፣ ዘጠኝ የልጅ ልጆችና አሥር የልጅ ልጅ ልጆች አሏቸው።
ምዕራፍ 1 ተጠናቋል
የደራሲው የሕይወት ታሪክ