ምዕራፍ 6 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
የዚሁ ቀጣይ
ሕይወታቸውን በቅድስና ልምምድ ላሳለፉት ለእነዚህ ሰዎች፣ ከቅናት የተነሣ ብዙ ውርደትንና ሥቃይን ታግሠው እጅግ መልካም ምሳሌ የሆኑልን እጅግ ብዙ የተመረጡ ሰዎች ይጨመራሉ። ከቅናት የተነሣ ዳናይዶችና ዲርቄዎች የተባሉት እነዚያ ሴቶች ተሰደው፣ አስፈሪና ሊነገር የማይችል ሥቃይ ከተቀበሉ በኋላ የእምነታቸውን ሩጫ በጽናት ፈጸሙ፤ በሥጋ ደካሞች ቢሆኑም የከበረ ዋጋን ተቀበሉ። ቅናት ሚስቶችን ከባሎቻቸው አራቅቶአል፤ የአባታችንንም የአዳምን፦ «ይህች አሁን አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት» የሚለውን ቃል ለውጦአል። ቅናትና ጠብ ታላላቅ ከተሞችን ገለበጡ፤ ኃያላን ሕዝቦችንም ከሥር ነቀሉ።
ምዕራፍ 6 ተጠናቋል
የዚሁ ቀጣይ