ምዕራፍ 39 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
ለትዕቢት ምክንያት የለም
ጥበብም ትምህርትም የሌላቸው ሰነፎችና የማያስተውሉ ሰዎች በገዛ አሳባቸው ራሳቸውን ከፍ ለማድረግ ተጣድፈው ይዘብቱብናል፥ ያላግጡብናልም። ሟች ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል? ወይስ ከአፈር ለተሠራ ምን ብርታት አለው? እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፦ «በዓይኔ ፊት መልክ አልነበረም፤ ድምፅንና ቃልን ብቻ ሰማሁ፦ እንግዲህ ምንድር ነው? ሰው በጌታ ፊት ንጹሕ ይሆናልን? ወይስ እንዲህ ያለው በሥራው ነቀፋ የሌለበት [ሆኖ ይቈጠራል]? እርሱ በባሪያዎቹ አይታመንም፥ መላእክቱንም እንኳ በጠማማነት ከሶአቸዋልና። ሰማይ በፊቱ ንጹሕ አይደለም፤ ይልቁንስ እኛ ራሳችን ከተሠራንበት ከዚያው ጭቃ በተሠሩ ቤቶች የሚኖሩትማ እንዴት ያንሳሉ! እንደ ብል መታቸው፤ ከጥዋትም እስከ ማታ አይጸኑም። ራሳቸውን ሊረዱ ስላልቻሉ ጠፉ። እፍ አለባቸው፥ ሞቱም፤ ጥበብ አልነበራቸውምና። አሁን ግን የሚመልስልህ እንዳለ ጥራ፤ ወይም ከቅዱሳን መላእክት ወደ አንዱ ትመለከት እንደ ሆነ። ቍጣ ሰነፉን ያጠፋልና፥ ቅንዓትም የሳተውን ይገድላል። ሰነፎች ሥር ሲሰድዱ አየሁ፤ መኖሪያቸው ግን ወዲያው ተበላ። ልጆቻቸው ከደኅንነት ይራቁ፤ ከእነርሱ በሚያንሱት ደጅ ፊት ይናቁ፥ የሚያድንም አይኑር። ለእነርሱ የተዘጋጀውን ጻድቃን ይበሉታልና፤ እነርሱም ከክፉ አይድኑም።»
ምዕራፍ 39 ተጠናቋል
ለትዕቢት ምክንያት የለም