ምዕራፍ 24 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
እግዚአብሔር ትንሣኤ እንደሚሆን በተፈጥሮ ዘወትር ያሳየናል
ወዳጆች ሆይ፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን በማስነሣት በኵራት ያደረገው ጌታ፣ ወደ ፊት ትንሣኤ እንደሚሆን ዘወትር እንዴት እንደሚያስረዳን እናስብ። ወዳጆች ሆይ፥ በየጊዜው እየሆነ ያለውን ትንሣኤ እንመልከት። ቀንና ሌሊት ትንሣኤን ይነግሩናል። ሌሊት ወደ እንቅልፍ ይወርዳል፥ ቀንም ይነሣል፤ ቀን [ደግሞ] ያልፋል፥ ሌሊትም ይመጣል። የ[ምድርን] ፍሬዎች እንመልከት፤ እህል እንዴት እንደሚዘራ እንይ። ዘሪው ወጥቶ በመሬት ላይ ይጥለዋል፤ ዘሩም እንዲህ ተበትኖ በምድር ላይ ሲወድቅ ደረቅና ራቁት ቢሆንም ቀስ በቀስ ይፈርሳል። ከዚያም ከመፍረሱ የተነሣ የጌታ የመግቦቱ ታላቅ ኃይል እንደ ገና ያስነሣዋል፤ ከአንድም ዘር ብዙዎች ተነሥተው ፍሬ ያፈራሉ።
ምዕራፍ 24 ተጠናቋል
እግዚአብሔር ትንሣኤ እንደሚሆን በተፈጥሮ ዘወትር ያሳየናል