ምዕራፍ 19 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
እነዚህን ምሳሌዎች በመከተል ሰላምን እንሻ
እንዲህ ያሉ ታላላቅና የከበሩ ሰዎች ትሕትናና እግዚአብሔርን በመምሰል የሆነው መገዛታቸው እኛን ብቻ ሳይሆን ቃሎቹን በፍርሃትና በእውነት የተቀበሉትን፣ ከእኛ በፊት የነበሩትን ትውልዶች ሁሉ የተሻሉ አድርጎአቸዋል። ስለዚህ ይህን ያህል ብዙ ታላላቅና የከበሩ ምሳሌዎች በፊታችን ስላሉ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ግብ ሆኖ በፊታችን ወደ ተቀመጠው ሰላም ልምምድ እንደ ገና እንመለስ፤ ወደ ዓለማት አባትና ፈጣሪ አትኩረን እንመልከት፤ ታላላቆቹንና እጅግ የሚበልጡትን የሰላም ስጦታዎቹንና በረከቶቹን አጥብቀን እንያዝ። በአእምሮአችን እናስተውለው፤ በነፍሳችንም ዓይኖች ወደ ታጋሹ ፈቃዱ እንመልከት። ለፍጥረቱ ሁሉ ምን ያህል ከቍጣ የራቀ እንደ ሆነ እናስብ።
ምዕራፍ 19 ተጠናቋል
እነዚህን ምሳሌዎች በመከተል ሰላምን እንሻ