ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈው የቀሌምንጦስ የመጀመሪያ መልእክት
ከሁከት አነሣሾች ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል

ምዕራፍ 14 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ

ከሁከት አነሣሾች ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በትዕቢትና በሁከት የአስጸያፊ ፉክክር መሪዎች የሆኑትን ከመከተል ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ትክክልና ቅዱስ ነው። ጠብንና ግርግርን ለማነሣሣት ተነሥተው ከመልካም ነገር ሊያርቁን የሚሹ ሰዎችን ፈቃድ በችኮላ ብንከተል ትንሽ ያይደለ ጉዳት፣ ይልቁንም ታላቅ አደጋ ይደርስብናልና። እንደ ፈጣሪያችን ርኅራኄና ቸርነት ምሳሌ እርስ በርሳችን ቸሮች እንሁን። እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና፦ «ቸሮች በምድር ይኖራሉ፥ ነውር የሌለባቸውም በእርሷ ላይ ይቀራሉ፤ ዓመፀኞች ግን ከፊቷ ይጠፋሉ።» ደግሞም [መጽሐፍ] እንዲህ ይላል፦ «ኃጢአተኛን ከፍ ከፍ ብሎ፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ተነሥቶ አየሁት፤ አለፍሁ፥ እነሆም፥ አልነበረም፤ ስፍራውንም በትጋት ፈለግሁ፥ አላገኘሁትም። ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም ተመልከት፤ ለሰላማዊ ሰው ቅሬታ አለውና።»

ገጽ 1 / 1 · 1 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል
ቀዳሚ ቀጣይ