ምዕራፍ 13 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
የትሕትና ምክር
ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ ትዕቢትንና ኩራትን ሁሉ፣ ስንፍናንና ቍጣንም አስወግደን ትሑታን እንሁን፤ እንደ ተጻፈውም እናድርግ (መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፦ «ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በባለ ጠግነቱ አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካ እርሱን በትጋት በመፈለግና ፍርድንና ጽድቅን በማድረግ በጌታ ይመካ»)፤ ይልቁንም የዋህነትንና ትዕግሥትን ሲያስተምረን የተናገራቸውን የጌታ የኢየሱስን ቃሎች እናስብ። እንዲህ ብሎአልና፦ «ምሕረትን ታገኙ ዘንድ መሐሪዎች ሁኑ፤ ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ፤ እንደምታደርጉ እንዲሁ ይደረግላችኋል፤ እንደምትፈርዱ እንዲሁ ይፈረድባችኋል፤ ቸርነትን እንደምታደርጉ እንዲሁ ቸርነት ይደረግላችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ በዚያው ይሰፈርላችኋል።» በዚህ ትእዛዝና በእነዚህ ሥርዓቶች፣ በትሕትና ሁሉ ለቅዱስ ቃሎቹ እየታዘዝን እንመላለስ ዘንድ ራሳችንን እናጽና። ቅዱሱ ቃል እንዲህ ይላልና፦ «ከትሑትና ከሰላማዊ፥ በቃሌም ከሚንቀጠቀጥ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?»
ምዕራፍ 13 ተጠናቋል
የትሕትና ምክር