አንድነትና ኅብረት
ርዕሱ

ምዕራፍ 3 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ

ርዕሱ

«የሰሎሞን መኃልየ መኃልይ።»

ይህ መጽሐፍ ብቸኛው መኃልየ መኃልይ፣ ማለትም የመዝሙሮች መዝሙር፣ ቢባል የተገባው ነው! እንደ እርሱ ያለ መዝሙር የለም። በትክክል ሲነበብ፣ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል ከምድራዊ ነገሮች ደስታ እጅግ የላቀ ሐሤት ወደ ልብ ያመጣል። ይህ መዝሙር ጸጋ ብቻ ሊያስተምረው፣ ተሞክሮ ብቻ ሊማረው የሚችል መዝሙር ነው ተብሎ በሚገባ ተነግሮአል። አዳኛችን ቅርንጫፍ ከወይኑ ግንድ ጋር ስላለው አንድነት ከተናገረ በኋላ እንዲህ ብሎ ይጨምራል፦ «ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ» (ዮሐንስ 15:11)። የተወደደው ደቀ መዝሙርም፣ እርሱ ይደሰትበት የነበረውን ኅብረት እንድንካፈል፣ «ከመጀመሪያው የነበረውን»፣ «ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን» እርሱን በመጻፍ እንዲህ ይላል፦ «ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን»። ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆንና በክርስቶስ መኖር የማያስገኙት ምን አለ? ሰላም፣ ፍጹም ሰላም፤ ዕረፍት፣ የማያቋርጥ ዕረፍት፤ ለጸሎታችን ሁሉ መልስ፤ በጠላቶቻችን ሁሉ ላይ ድል፤ ንጹሕና ቅዱስ ኑሮ፤ ዘወትር እየጨመረ የሚሄድ ፍሬያማነት። እነዚህ ሁሉ፣ አዎን ሁሉ፣ በክርስቶስ የመኖር አስደሳች ውጤቶች ናቸው። ይህን አንድነት ማጥለቅ፣ ይህንም በእርሱ መኖር የበለጠ የማያቋርጥ ማድረግ የዚህ የከበረ መጽሐፍ ተግባራዊ ጥቅም ነው።

ገጽ 1 / 1 · 1 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል
ቀዳሚ ቀጣይ