እስኪመጣ ድረስ
የመግቢያ ማስታወሻ

ምዕራፍ 1 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ

የመግቢያ ማስታወሻ

የመግቢያ ማስታወሻ።

ሚስተር ስፐርጀን ለብዙ ዓመታት በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር፥ ሕመም ካልከለከለው በቀር፥ በየሰንበቱ የጌታን ራት ሥርዓት መፈጸም የዘወትር ልማዱ ነበር። ይህም ከሐዋርያት ልማድ ጋር የሚስማማ እንደ ሆነ ያምን ነበር፤ የጌታውን ትእዛዝ፥ «ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት» የሚለውን፥ አብዝቶ በታዘዘ መጠን አዳኙ ይበልጥ ውድ እንደሚሆንለት፥ የመታሰቢያው በዓል ራሱም ዓመታት እያለፉ በሄዱ ቍጥር ይበልጥ የሚረዳና የሚያስተምር እንደ ሆነ ደጋግሞ ይመሰክር ነበር።

በዚህ መጽሐፍ ከታተሙት ንግግሮች አንዳንዶቹ በሜትሮፖሊታን ታበርናክል ለሺህ ለሚቈጠሩ ቍርባን ተቀባዮች የተነገሩ ናቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በሜንቶን በሚስተር ስፐርጀን የእንግዳ መቀበያ ክፍል በቍርባን ማዕድ ዙሪያ ለተሰበሰቡ፥ ከልዩ ልዩ ቤተ እምነቶችና ከልዩ ልዩ ሕዝቦች ለመጡ ጥቂት ክርስቲያኖች የቀረቡ ናቸው። መልእክቶቹ ብዙ ዓይነት ርዕሶችን ይዳስሳሉ፤ ሁሉም ግን የተቈረሰው እንጀራና የተሞላው ጽዋ ቀላል ነገር ግን ትርጕም ያላቸው ምልክቶቹ ስለ ሆኑለት ስለ ታላቁ የማስተስረያ መሥዋዕት በመጠኑም ሆነ በሙላት ይናገራሉ።

ሚስተር ስፐርጀን ከቍርባን መልእክቶቹ የተመረጡትን ለማሳተም አስቦ ነበር፤ ስለዚህ ይህ መጽሐፍ ገና ለጥቂት ጊዜ በዚህ በምድር ለሚቆዩት በክርስቶስ ወንድሞቹና እኅቶቹ ካወረሳቸው ውድ የጽሑፍ ቅርሶች እንደ አንዱ ሊቈጠር ይችላል። እነዚህ አጫጭር ስብከቶች የብዙ አማኞችን መንፈሳዊ ሕይወት ለማጥለቅ መሣሪያ እንደሚሆኑ፥ ሥርዓቱን የመምራት መብትና ኃላፊነት ላላቸውም ለማሰላሰልና ለንግግር የሚስማሙ ርዕሶችን እንደሚጠቁሙ ተስፋ ይደረጋል።

ጨርሰዋል፦ የመግቢያ ማስታወሻ

ቀጣይ