ምዕራፍ 27 · 7 ደቂቃ ንባብ · 9 ደቂቃ ማዳመጥ
አባሪ ሀ፦ ጆርጅ ሙለርን የቀረጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች
አንዳንድ ጎልተው የሚታዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዛትና የተስፋ ቃላት በዚህ የእግዚአብሔር ሰው ላይ እጅግ ልዩ ተጽዕኖ ስለ ነበራቸው፥ ብዙ ጊዜም የሕይወት ጐዳናውን የመሩ ሆነው ስለ ተገኙ፥ የመዝሙር 119:105ን እውነት በግልጥ ያሳያሉ፦
«ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው።»
በመንገድ መለያያ ላይ ትክክለኛውን አቅጣጫ እያሳዩ የእግዚአብሔር የመንገድ ምልክቶች የሆኑለት እነዚያ ጥቅሶች፥ በተቻለ መጠን እርሱን በረዱበት ቅደም ተከተል እዚህ ቀርበዋል። እነርሱን ማጥናት የሕይወት ጉዞውን በአጭሩ የሚያሳይ አንድ ዓይነት መንፈሳዊ የሕይወት ታሪክ ይሆናል። ተጽዕኖአቸው እጅግ ጎልቶ እንደ ታየ የሚታወቁትን አንዳንድ ጥቅሶች በዐቢይ ፊደላት አስቀምጠናቸዋል። ሰያፍ ፊደላቱ የራሱ ናቸው።
«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።» (ዮሐንስ 3:16)
«በሰው የሚታመን ሥጋንም ክንዱ የሚያደርግ ሰው ርጉም ነው።» (ኤርምያስ 17:5)
«እናንተ ቅዱሳኑ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ለሚፈሩት አንዳች አይጎድልባቸውምና።» (መዝሙር 34:9)
«እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ» (ሮሜ 13:8)።
«ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።» (ማቴዎስ 6:33)
«መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን» (2ኛ ጢሞቴዎስ 3:15)።
«ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።» (ማቴዎስ 7:7, 8)
«አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።» (ዮሐንስ 14:13, 14)
«ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ.... ለነገ አትጨነቁ» (ማቴዎስ 6:25-34)።
«ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥» ስለ ትምህርቱ ያውቃል (ዮሐንስ 7:17)።
«እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል» (ዮሐንስ 8:31, 32)።
«ጃንደረባውም። እነሆ ውኃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው? አለው። ፊልጶስም። በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል አለው። መልሶም። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ አለ። ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም።» (የሐዋርያት ሥራ 8:36-38)
«ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?» እንግዲህ «ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።» (ሮሜ 6:3, 4)
«ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን» (የሐዋርያት ሥራ 20:7)።
«ወንድሞቼ ሆይ፥ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ። የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ። አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ ብትሉት፥ ድሀውንም። አንተስ ወደዚያ ቁም ወይም ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን? ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን?» (ያዕቆብ 2:1-6)
«እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን» (ሮሜ 12:6)።
«ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።» (1ኛ ቆሮንቶስ 12:11)
«በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም።» (ፊልጵስዩስ 4:17)
«ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤».... «ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤.... የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤.... ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።» (ማቴዎስ 6:25-32)
«ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ» (ማቴዎስ 6:19)።
«ያላችሁን ሽጡ ምጽዋትም ስጡ» (ሉቃስ 12:33)።
«ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም።» (ዮሐንስ 3:27)
«እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል።» (የሐዋርያት ሥራ 15:14። ማቴዎስ 13:24-30, 36-43ን አነጻጽሩ።)
«ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።.... ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።» (2ኛ ጢሞቴዎስ 3:1, 13)
«ከመካከላቸው ውጡ፥ ተለዩም፥ ይላል ጌታ፤ ርኩስንም አትንኩ።» (2ኛ ቆሮንቶስ 6:14-18)
«በኃይልና በብርታት አይደለም፥ በመንፈሴ ነው እንጂ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።» (ዘካርያስ 4:6)
«ጸጋዬ ይበቃሃል» (2ኛ ቆሮንቶስ 12:9)።
«እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር።» «እያንዳንዱ በተጠራበት እንደዚሁ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኑር።» (1ኛ ቆሮንቶስ 7:20, 24)
«የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማል።» (2ኛ ጢሞቴዎስ 3:16)
«አፍህን አስፋ፥ እሞላዋለሁም።» (መዝሙር 81:10)
«ጊዜዬ ገና አልደረሰም» (ዮሐንስ 2:4)።
«ሕፃንም ይዞ በመካከላቸው አቆመው አቅፎም። እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው።» (ማርቆስ 9:36, 37)
«ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።» (ሮሜ 12:18)
«እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።» (ዕብራውያን 12:10, 11)
«የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።» (ማርቆስ 11:24)
«በእርሱም የሚያምን አያፍርም» (1ኛ ጴጥሮስ 2:6)።
«ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፥ ሥጋ ሁሉ ወደ አንተ ይመጣል።» (መዝሙር 65:2)
«እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፥ ኑ ስሙ፥ ለነፍሴ ያደረገላትን እነግራችኋለሁ።» (መዝሙር 66:16)
«የድሀ አደጎች አባት» (መዝሙር 68:5)።
«ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፥ በዘለፋውም አትታክት።» (ምሳሌ 3:11)
«አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል።» (መዝሙር 103:13)
«ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።» (ዕብራውያን 13:8)
«ነገ ለራሱ ይጨነቃል» «ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።» (ማቴዎስ 6:34)
«እስከዚህ ድረስ እግዚአብሔር ረዳን።» (1ኛ ሳሙኤል 7:12)
«እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤»
«በእርሱ የሚታመን ሰው ብፁዕ ነው!» (መዝሙር 34:8)
«ስቡ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።» (ዘሌዋውያን 3:16)
«እኔ ድሀና ችግረኛ ነኝ፤ እግዚአብሔር ግን ያስብልኛል።» (መዝሙር 40:17)
«በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።» (መዝሙር 37:4)
«በልቤ ዓመፃን ብመለከት ጌታ አይሰማኝም።» (መዝሙር 66:18)
«እግዚአብሔር ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ እወቁ፤ ወደ እርሱ በጠራሁ ጊዜ እግዚአብሔር ይሰማኛል።» (መዝሙር 4:3)
«ይሖዋ ይርኤ።» (እግዚአብሔር ያዘጋጃል።) (ዘፍጥረት 22:14)
«እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤ ስለዚህ በድፍረት። ጌታ ይረዳኛል» እንላለን። (ዕብራውያን 13:5, 6)
«እጅን ከሚማቱ፥ ለዕዳም ዋስ ከሚሆኑ ጋር አትሁን።» (ምሳሌ 22:26)
«ዋስትናን የሚጠላ ተማምኖ ይኖራል።» (ምሳሌ 11:15)
«ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን እከፍላለሁ፥ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ። ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ በዚህ ልክ ፍቅራችሁ የሚያንስ ነውን?» (2ኛ ቆሮንቶስ 12:15)
«በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ» (ገላትያ 3:26)።
«እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።» (1ኛ ጴጥሮስ 5:7)
«በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።» (ፊልጵስዩስ 4:6)
«ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?» (ዮሐንስ 11:40)
«እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።» (ሮሜ 8:28)
«የምድር ሁሉ ፈራጅ ቅን ፍርድን አያደርግምን?» (ዘፍጥረት 18:25)
«መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ (ሕፃናት) ላሉ ናትና» (ማቴዎስ 19:14)።
«ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?» (ሮሜ 8:32)
«በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው» (ያዕቆብ 1:17)።
«የአንበሳ ደቦሎች ይቸገራሉ፥ ይራባሉም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።» (መዝሙር 34:10)
«የሚበትን አለ፥ ይጨመርለትማል፤ የሚገባውን የሚነፍግም አለ፥ ወደ ድህነትም ብቻ ይሄዳል። ለጋስ ነፍስ ትጠግባለች፤ የሚያጠጣም ራሱ ደግሞ ይጠጣል።» (ምሳሌ 11:24, 25)
«ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።» (ሉቃስ 6:38)
«ለጋስ ሰው የልግስናን ነገር ያስባል፥ በልግስናውም ይጸናል።» (ኢሳይያስ 32:8)
«ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ» (ማርቆስ 14:7)።
«እንግዲህ ለእናንተ ያለው መልካም ነገር አይሰደብ» (ሮሜ 14:16)።
«ገርነታችሁ» (እሺ ባይነታችሁ) «ለሰው ሁሉ ይታወቅ።» (ፊልጵስዩስ 4:5)
«ወንድሞቼ ሆይ፥ ልዩ ልዩ ፈተና (ማለትም መከራ) ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ ታውቃላችሁና። ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።» (ያዕቆብ 1:2-4)
«በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ። በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።» (ምሳሌ 3:5, 6)
«የቅኖች ቅንነት ትመራቸዋለች፤ የወስላቶች ጠማማነት ግን ታጠፋቸዋለች።» (ምሳሌ 11:3)
«ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ይጸናልሃል።» (ምሳሌ 16:3)
«እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።» (ሮሜ 12:3)
«እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ አይዞህ፥ እርሱም ልብህን ያጸናል፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ እላለሁ።» (መዝሙር 27:14)
«ከታገሰ በኋላ ተስፋውን አገኘ።» (ዕብራውያን 6:15)
«እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።» (ዮሐንስ 16:23)
«በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል።» (2ኛ ቆሮንቶስ 9:6)
«በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።» (1ኛ ቆሮንቶስ 6:20)
«ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፤ አቤቱ፥ የሚፈልጉህን አልተውሃቸውምና።» (መዝሙር 9:10)
«በአንተ ታምኖአልና አሳቡ በአንተ የጸናውን በፍጹም ሰላም ትጠብቀዋለህ። በጌታ በእግዚአብሔር የዘላለም ኃይል አለና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።» (ኢሳይያስ 26:3, 4)
«በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም።» (2ኛ ቆሮንቶስ 8:12)
«ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።» (1ኛ ቆሮንቶስ 15:58)
«ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።» (ገላትያ 6:9)
«አቤቱ፥ ለሚፈሩህ ያኖርኻት፥ በሰው ልጆችም ፊት በአንተ ለሚታመኑ ያደረግኻት ቸርነትህ እንዴት ብዙ ናት!» (መዝሙር 31:19)
«አንተ ቸር ነህ፥ መልካምም ታደርጋለህ።» (መዝሙር 119:68)
«አቤቱ፥ ፍርድህ ቅን እንደ ሆነ፥ በታማኝነትም እንዳስጨነቅኸኝ አወቅሁ።» (መዝሙር 119:75)
«ዘመኖቼ በእጅህ ናቸው።» (መዝሙር 31:15)
«እግዚአብሔር አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነውና፤ እግዚአብሔር ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም።» (መዝሙር 84:11)
«ደግፈኝ፥ እድናለሁም።» (መዝሙር 119:117)
«እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።» (ራእይ 22:12)
«ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው» (የሐዋርያት ሥራ 20:35)።
«የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን» (ማቴዎስ 6:11)።
«ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው» (ኤፌሶን 3:20)።
«የሚያከብሩኝን አከብራለሁ።» (1ኛ ሳሙኤል 2:30)
«ይህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።» (1ኛ ጴጥሮስ 1:7)