ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈው የቀሌምንጦስ የመጀመሪያ መልእክት
የቆሮንቶስ ሰዎች ሰላም እንደ ተመለሰ መልእክት እንዲልኩ ተመከሩ

ምዕራፍ 59 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ

የቆሮንቶስ ሰዎች ሰላም እንደ ተመለሰ መልእክት እንዲልኩ ተመከሩ

ወደ እናንተ የላክናቸውን እነዚህን መልእክተኞቻችንን፥ ቀላውዴዎስ ኤፌቦስንና ዋሌርዮስ ቢቶን ከፈርዶናጥስ ጋር፥ በሰላምና በደስታ ፈጥናችሁ ወደ እኛ መልሱአቸው፤ ይኸውም እጅግ የምንመኘውንና የምንናፍቀውን [በመካከላችሁ ያለውን] ሰላምና ስምምነት ፈጥነው እንዲያበሥሩን፥ እኛም በመካከላችሁ ተመልሶ በጸናው መልካም ሥርዓት ፈጥነን ደስ እንዲለን ነው። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ በእርሱም በኩል በእግዚአብሔር ከተጠሩት በየስፍራው ካሉት ሁሉ ጋር ይሁን፤ በእርሱ በኩል ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና፥ ኃይልና ግርማ፥ የዘላለምም ግዛት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን። አሜን።

ምዕራፍ 59 ተጠናቋል

የቆሮንቶስ ሰዎች ሰላም እንደ ተመለሰ መልእክት እንዲልኩ ተመከሩ

ገጽ 1 / 1 · 1 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል
ቀዳሚ