ምዕራፍ 23 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
ትሑታን ሁኑ፤ ክርስቶስም ዳግመኛ እንደሚመጣ እመኑ
ሁሉን መሐሪና ቸር የሆነው አብ ለሚፈሩት [የርኅራኄ] አንጀት አለው፤ በቅን ልብ ወደ እርሱ ለሚመጡትም ሞገሱን በደግነትና በፍቅር ይሰጣል። ስለዚህ ሁለት ልብ አንሁን፤ ነፍሳችንም ከእጅግ ታላቅና ክቡር ስጦታዎቹ የተነሣ አትታበይ። «ሁለት አሳብ ያላቸው፣ በልባቸውም የሚጠራጠሩ ጐስቋሎች ናቸው፤ እነርሱም፦ ይህን ነገር በአባቶቻችን ዘመን እንኳ ሰምተናል፤ እነሆ ግን አርጅተናል፤ ከእነዚህም አንዳቸውም አልደረሱብንም የሚሉ ናቸው» ተብሎ የተጻፈው ከእኛ ይራቅ። እናንተ ሰነፎች! ራሳችሁን ከዛፍ ጋር አስተያዩ፤ ለምሳሌ የወይን ግንድን ውሰዱ። በመጀመሪያ ቅጠሉን ያረግፋል፤ ከዚያም ያቈጠቍጣል፤ ቀጥሎም ቅጠል ያወጣል፤ ከዚያም ያብባል፤ ከዚያ በኋላ ጎምዛዛው የወይን ፍሬ ይመጣል፤ ቀጥሎም የበሰለው ፍሬ ይከተላል። የዛፍ ፍሬ በጥቂት ጊዜ እንዴት እንደሚበስል ታያላችሁ። በእውነት ፈቃዱ ፈጥኖና በድንገት ይፈጸማል፤ መጽሐፍም ደግሞ፦ «ፈጥኖ ይመጣል፥ አይዘገይምም»፤ ደግሞም፦ «ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትጠብቁትም ቅዱሱ ይመጣል» ብሎ ይመሰክራል።
ምዕራፍ 23 ተጠናቋል
ትሑታን ሁኑ፤ ክርስቶስም ዳግመኛ እንደሚመጣ እመኑ