ምዕራፍ 22 · 1 ደቂቃ ንባብ · 1 ደቂቃ ማዳመጥ
እነዚህ ምክሮች በክርስቲያን እምነት ጸንተዋል
በክርስቶስ ያለው እምነት እነዚህን [ምክሮች] ሁሉ ያጸናል። እርሱ ራሱ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይለናልና፦ «ልጆች ሆይ፥ ኑ፥ ስሙኝ፤ ጌታን መፍራት አስተምራችኋለሁ። ሕይወትን የሚሻ፥ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚወድ ሰው ማን ነው? ምላስህን ከክፉ ከንፈሮችህንም ተንኰልን ከመናገር ከልክል። ከክፉ ራቅ፥ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን ሻ፥ ተከተለውም። የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል። የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው፥ መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ። ጻድቁ ጮኸ፥ ጌታም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።» «የኃጥኣን መቅሠፍት ብዙ ነው፤ በጌታ ተስፋ የሚያደርጉትን ግን ምሕረት ይከብባቸዋል።»
ምዕራፍ 22 ተጠናቋል
እነዚህ ምክሮች በክርስቲያን እምነት ጸንተዋል