ጸሎት — የሕይወት ትርታ
የእርሱ መመለስ!

ምዕራፍ 9 · 1 ደቂቃ ንባብ

የእርሱ መመለስ!

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመገናኘት ራስህን አዘጋጅ!

«በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።» ሉቃስ 21:25-28። ዛሬ የት እንዳለንና አሕዛብ የሚፈረዱበት ጊዜ ምን ያህል እንደ ቀረበ የሚያሳዩን ብዙ ምልክቶች አሉ። አሁን የትም ብትሆን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በቅርቡ እንደሚመጣ ሁልጊዜ አስታውስ።

አንዳንዶች አምነው መመለሱን በጉጉት ይጠባበቃሉ፤ ሌሎች ደግሞ ተጠራጣሪዎች ናቸው፤ አይጠብቁትምም። እርሱ ግን ይመጣል፤ ስለዚህ ራስህን ለእርሱ አዘጋጅ። የሚመጣው «…መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ» (2ኛ ጢሞቴዎስ 4:8)፣ ማለትም ለእርሱ ተዘጋጅተው ላሉት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ መመለሱን እየተጠባበቁ ያሉት ብፁዓን እንደ ሆኑ ይናገራል (ሉቃስ 12:37)።

በትምህርት ቤትም ሆነ በቤት ወይም በሌላ በማንኛውም ስፍራ ስትሆን፣ መመለሱ በማንኛውም ቅጽበት ሊሆን እንደሚችል አድርገህ ኑር፤ በእርግጥም በማንኛውም ቅጽበት ሊሆን ይችላልና። 1ኛ ቆሮንቶስ 15:52 እንዲህ ይለናል፦ «በቅጽበት፥ በዓይን ጥቅሻ፥ በኋለኛው መለከት፤ መለከት ይነፋልና፥ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፥ እኛም እንለወጣለን።» ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ካረገ ወደ ሁለት ሺህ ዓመት ሊሞላው ነው። ስለ መምጣቱ የተነገሩት ትንቢቶች በዓይናችን ፊት እየተፈጸሙ ነው። እርሱ፦ «አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ…» ብሏል (ራእይ 22:20)።

ዛሬ ያለው ዓለም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የጭካኔ፣ የዓመፅና የሽብርተኝነት ዓለም እንደ ሆነ አኃዛዊ መረጃዎች ያሳያሉ።

የሕይወት ፈተናዎች ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ዛሬ ከብደዋል። ስለዚህ ሳታስበው አትያዝ። በክርስቶስ ኑር፤ በጽድቅ ተመላለስ፤ ለእርሱም መኖርህን ቀጥል። ወንጌልን በመስበክና ነፍሳትን ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማምጣት ዓለምህን በወንጌል አብራ። ዋጋህ ታላቅ ነው።

ዓለም እየተለዋወጠች ሳለ ለግፊቷ እጅ አትስጥ፤ በዓለም ካለው ይልቅ በአንተ ያለው ታላቅ ነውና። ክርስቶስ በሁሉ ነገር ላይ ሥልጣን ሰጥቶሃል። የማትናወጥ ሁን። ከዓለም ሥርዓቶች በላይ ኑር።

ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል! ይህ ተረት ወይም አፈ ታሪክ አይደለም፤ ሊሆን ቀርቦአል!

ወንጌል እስከ ምድር ዳርቻ እስኪደርስ ድረስ ጊዜህን፣ ሀብትህንና ጉልበትህን ለማዳረሱ ሥራ ስጥ። ራስህን አዘጋጅ፤ ሌሎችም ለቤተ ክርስቲያን መነጠቅ እንዲዘጋጁ እርዳ።

ገጽ 1 / 1 · 1 ደቂቃ በምዕራፉ ቀርቷል